እንኳን ወደ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በደህና መጡ

ኢሲኤ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን የሚቆጣጠር፣የተስተካከለ እና አቅምን የሚገነባ የመንግስት ድርጅት ነው።

ስለ እኛ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን (ኢሲኤ) በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለውን የመቆጣጠር፣ የማሳለጥ እና አቅምን ለማሳደግ የሚሰራ የመንግስት ድርጅት ነው። ተልእኮው ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪን የሚያበረታታ የቁጥጥር አገልግሎቶችን መስጠት፣ ፕሮጀክቶችን በወቅቱ፣ በበጀት ውስጥ እና በተቀመጡት ደረጃዎች መሰረት መፈፀምን ማረጋገጥ ሲሆን ሁሉም የአካባቢ እና ማህበራዊ ደህንነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።

የእኛ አገልግሎቶች

ዋና ኃላፊነቶች

ግጭት አፈታት

በኮንስትራክሽን ኢንዳስትሪው ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በአማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴ በውስጥ ግልግል (Arbitration) በመጠቀም እንዲፈቱ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ኦዲትና ኢንስፔክሽን

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን እና የምዝገባ ፍቃድ ሰርተፊኬሽን ላይ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን በማድረግ የተገኙ ክፍተቶችን ርምት እንዲደረግባቸው የሚያደርግ አገልግሎት ነው፡፡

ፕሮጀክት ዲዛይን ቁጥጥር

ጥራታቸው የተረጋገጠ የሕንጻ፣ የውሃና ኢነርጂ፣ የትራንስፖርትና ኮሚኒኬሽን ፕሮጀክት ሥራዎች ዲዛይኖች እንዲኖሩ ማድረግ ሲሆን የቅድመ ግንባታ ሰነዶች ላይ ሕጎች ተፈጻሚ መሆናቸውን በመቆጣጠር፣ በማረጋገጥ እና በማጽደቅ የተገኙ ክፍተቶችን ርምት እንዲደረግባቸው በማድረግ ውጤታማ የግንባታ ዲዛይኖች እንዲኖሩ ማስቻል ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ መረጃ አናሊስስ እና ሲስተም ልማት

የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪውን መረጃ በመሰብሰብ፣ በማደራጀት እና በመተንተን ለቁጥጥር እና ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆን ወቅታዊና ተደራሽ መረጃን ማጎልበትና ማሰራጨት ነው፡፡ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን መረጃ አስተዳደር ስርዓቱን ለማሻሻል የሚያስችሉ የጥናት ሥራዎችን በማከናወን፣ ሶፍትዌሮችን በማልማት ኦቶሜት ማድረግ ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ኮድና ስታንዳርድ

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ሊያሳድጉ የሚችሉ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ከዓለም ዐቀፍ ስታንዳርዶች ጋር የተጣጣሙ የሕንጻ ግንባታና የመሠረተ ልማት ኮዶች፣ ስታንዳርዶች፣ አሠራሮችን ማዘጋጀት እና ቅንጅታዊ አሠራሮችን በማጎልበት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን የመፈጸም ዐቅም መገንባት ነው፡፡

ፕሮጀክቶች ግንባር ቁጥጥር

በመንግሥት እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚገነቡ የሕንጻ፣ የትራንስፖርትና ኮሚኒኬሽን፣ የውሃና ኢነርጂ ፕሮጀክቶችን እና የግንባታ ግብአቶችን፣ በታቀደላቸው ጊዜ፣ በተያዘላቸው ወጪ፣ በሚጠበቀው ጥራት እንዲሁም የአከባቢውን እና የሠራተኛውን ደኅንነትና ጤንነት ጠብቀው የግንባታ ሕጉን ኮድና ስታንዳርዱን አሟልተው መገንባታቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ምዝገባ ሰርተፊኬሽን

በኮንስትራክሽን ኢንዱሰትሪ የሚሰማሩ ኩባንያዎች (ሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች) እና ባለሙያዎችን በወጡ ዐዋጆች፣ደንቦች እና መመሪያዎች መሠረት ብቃታቸውን በማረጋገጥ እና ፕሮጀክቶችን የመመዝገብ ተግባር ነው፡፡
ራዕይ

በ2022 በተጠናከረ የቁጥጥር ስርዓት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በአፍሪካ ተወዳዳሪ ሆኖ ማየት!” Vision: To See Regulated & Most Competitive Construction Industry in Africa By 2030!

የኮንስትራክሽን ሥራዎች የአከባቢን እና የዜጎችን ጤንነትና ደህንነት የጠበቁና ምቹ መሆናቸውን በተቀመጡ ሕጎች፣ኮዶች እና ደረጃዎች መሠረት መከናወናቸውን የማረጋገጥ ሒደትን የሚመላክት ነው፡፡

ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት በመፍጠር እና ተፈጻሚነቱን በመረጋገጥ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከሀገር ውስጥ ገበያ ተሻግሮ በጊዜ፣በጥራት እና በወጪ ቆጣቢነት በአፍሪካ ተወዳዳሪ በመሆን የውጭ ምንዛሪ የማምጣት አቅም እንዲኖረው ማስቻልን የሚያመለክት ነው፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የግንባታ ፕሮጀክቶች በተገቢው ወጪ፣ጊዜ ጥራት መፈጸሙን እንዲሁም የዜጎችን፣የአካባቢ ደህንነትንና ጤንነትን መጠበቁን በማረጋገጥ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡
ልህቀት፣ የቡድን ስራ፣ ግልጽኝነት፣ ምሉዕነት፣ ቁርጠኝነት፣ ተጠያቂነት፣ ዘላቂነት