የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት ይፋ ሆነ
መስከረም 27/2018 (ኢኮባ):-
የኢት/ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያስለማው የግንባታ ቁጥጥር መረጃ ሶፍትዌር ስርአት(CRIS) እና የሳይበር ደህንነት አስተዳደር ስርአት ወደትግበራ ማስገቢያ ስነስርአት ላ የባለስልጣን ተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መስፍን ነገዎ ያስተላለፉት መልዕክት:-
👉ኹነቱ ልዩ የሚያደርገው በሀገራችን ነባር አኩሪ ታሪኮች ተርታ አብሪ ኮኮብ ሆኖ የሚኖር የህዳሴ ግድብ በተመረቀበት፣ የካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ ለምቶ የተበሰረበት፣ የጉባ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይፋ ተደርገው ወደትግበራ የተገባበት ፣ የኮንስትራክሽን ሴክተሩን ማላቅ የሚያስችል የትራንስፎርሜሽን ፍኖተካርታ ና ተያያዥ ኢንሼቲቮች ወደትግበራ የተገባበት ወቅት መሆኑ፣
👉ዛሬ ይፋ የተደረገው የግንባታ የግንባታ ቁጥጥር መረጃ ሶፍትዌር(CRIS) የዘርፉን ትራንስፎርሜሽን ፍኖተካርታ ኢንሼቲቮች እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 524/2022 የተሰጡትን ሃላፊነትና ስራዎች በግልጽ፣ በጥራት እና በብቃት ተፈጻሚነትን የሚያሳልጥ ነው፣
👉ስርአቱ ለሀገራችንና ለግንባታ ዘርፍ ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎትን ይሰጣል፣ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያረጋግጣል፣
👉እንዲሁም ተቋማዊ ውሳኔ በወቅቱ፣በጥራት የመስጠት አቅምን ይፈጥራል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ስርአትእንዲኖር ያስችላል
👉በአጠቃላይ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ ሚና አለው::
Official Launch Announcement
The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with INSA (Information Network Security Administration), is pleased to announce the successful launch of its new System Development Program.
A brief ceremony was held today to mark this important milestone, which reflects our continued commitment to digital transformation and improved public service delivery in the construction sector.
We extend our sincere appreciation to all partners and professionals who made this achievement possible.







