WELCOME TO ETHIOPIAN CONSTRUCTION AUTHORITY

የኢኮባ አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡

የኢኮባ አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡

(ኢኮባ፣ ነሐሴ 05 ቀን 2015 ዓ.ም)፡- የኢኮባ አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድን ውጤታማ ለማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ሰሞኑን አዳማ ከተማ ላይ በተካሄደው የአመራሮችና ሰራተኞች አጠቃላይ ስብሰባ ላይ የተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ግቦች እና ግቦችን ለማሳካት የተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ የተቋሙ ዕቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ለገሰ አቅርበዋል፡፡


ዕቅዱ ቀደም ሲል ከስራ ክፍሎች ጀምሮ በየደረጃው ተገምግሞ እና በተቋቋመ ቡድን አማካኝነት ይበልጥ ዳብሮ የተዘጋጀ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የቀረበውን የዕቅድ ሰነድ ተከትሎ የልዩ ልዩ ስራ ክፍሎች ሰራተኞችና አመራሮች የተካተቱበት ቡድኖች ተቋቁመው የጋራ ምክክር ተደርጎበታል፡፡ ቡድኖቹ ባቀረቡት የተጠቃለለ ሪፖርት መሰረት የዕቅድ ዘመኑን ውጤታማ ለማድረግ ቁርጠኛ የሆነ ተግባቦት ላይ ተደርሷል፡፡እንዲያም ሆኖ ትኩረት ያሻቸዋል የተባሉ ግብረ-መልሶችም ቀርበዋል፡፡ በዋናነትም በተቋሙ ወቅታዊ አደረጃጀት መሰረት አዲስ ለተፈጠሩ የስራ ክፍሎች ላይ በቂ ስልጠና ቢሰጥ ለተቀመጡ የዕቅድ ግቦች አፈፃፀም መሳካት ጠቃሚነቱን ገልፀዋል፡፡


በተጨማሪም የዕቅድ ዘመኑን ግቦች በውጤታማነት ለመፈፀም በሚደረገው ርብርብ የበጀት እና የሰው ኃይል መጣጣም ላይ ትኩረት የሚያሻቸው ስለመሆናቸውም ከቡድኖቹ ግብረመልሶች ቀርበዋል፡፡ ማብራሪያ የሚያሻቸው የግልጽነት ጥያቄዎችም ቀርበዋል፡፡ አሳታፊ፣ ግልጽ እና ተግባቦትን የፈጠሩ ሃሳቦች የተንፀባረቁበት የቡድኖቹን የውይይት ሪፖርት ተከትሎም ዋና ዳይሬክተሩ ኢ/ር መስፍን ነገዎ ግልፅ ባልሆኑ ነጥቦች ላይ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


የበጀት አመት ዕቅዱ በትግበራ ሂደት ላይ የሚገጥሙት ተግዳሮቶች እየተለዩና የማስተካከያ እርምጃዎች እየተወሰዱ ተግባራዊ እንደሚደረጉም ኢ/ር መስፍን ነገዎ አስገንዝበዋል፡፡ አጠቃላይ አመራሩና ሰራተኞች በደረሱበት የዝግጁነት፣ የቁርጠኝነት እና የተግባቦት ልክ መሰረት ውጤታማ ርብርብ እንዲያደርጉ አደራ ጭምር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


በተያያዘ ዜና የተቋሙ የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም የአካል ምልከታ ዳሰሳ ሰነድ ለውይይት ቀርቧል፡፡
የተቋሙ የዕቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ወንድወሰን ተፈራ ባቀረቡት የዳሰሳ ሰነዱ ላይ እንደተመለከተው የስራ ክፍሎች ያቀረቡት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተዓማኒነቱን የማረጋገጥ ስራ ተከናውኗል፡፡
በዚሁ መሰረትም ዳሰሳው የተካሄደባቸው የስራ ክፍሎች እና የግቦች አፈፃፀም ሪፖርት በአካል ምልከታው ተዓማኒ መሆናቸውን ተመልክቷል፡፡


የኢኮባ ሕዝብግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን

Previous ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት የተሾሙት ም/ዋና ዳይሬክተሮች ከተቋሙ አመራሮች ጋር ትውውቅ አካሄዱ::

Leave Your Comment

Bole, Addis Ababa,Ethiopia

Opening Hours:

Mon – Fri: 8:00 am – 6:00 pm

Calander

September 2024
M T W T F S S
 1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
30  

ECA News & Updates

The latest Ethiopian Construction Authority news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Ethiopian Construction Authority © 2020. All Rights Reserved
Designed & Developed by Kanenus Technologies 0973200216