የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ተገልጋዮችን በማስተናገድ ላይ ናቸው፡፡
በስነ-ምግባር የታነፀ አገልግሎት ክብር ነው !(ጳጉሜን 1 ቀን 2015 ዓ.ም)፡-በሕግ አካባሪነት ጥበብ የተቃኘ አገልግሎት፣ በአወንታዊ አመለካከት ጥራት የታጀበ አገልግሎት፤ በስራ አፍቃሪነት ባህል የተተገበረ አገልግሎት፤ ስነ-ምግባርንና መልካም ስብዕናን ከተላበሰ ልቦና የፈለቀ አገልግሎት ሰው የመሆን መገለጫዎች ናቸው፡፡ የክብር፣ የስብዕና፣ የቅንነት፣ የአስተዋይነት፣ የብስለት መገለጫዎች ናቸው፡፡በትህትና የተሞላ አገልግሎት ክብር ነው፡፡ በአገልግሎት ላይ የሚፈልቁ ትሁት ቃላት ቀላል እና አጭር ጊዜን […]
የመልካም አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
(ነሀሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም )፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የመልካም አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ሰነድ ላይ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡የመልካም አገልግሎት መስፈን ለሀገራዊ ማህበረ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚጫወተው ሚና የላቀ በመሆኑ በዚህ ረገድ እንደየተቋማት ተጨባጭ ሁኔታ የታዩ በጎ ገፅታዎች የመኖራቸውን ያህል ችግሮችም መስተዋላቸው ተመልክቷል፡፡ሀገራዊ የልማትእቅዶችን […]
ኢኮባ አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም እና ቀጣይ ዕቅድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡
(ኢኮባ፡-ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም) ለኢኮባ አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም እና ቀጣይ ዕቅድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡ግንዛቤ ማስጨበጫው ሀገራዊ የ10 ዓመት የመጀመሪያው መካከለኛ ዘመን ( 2013-2015 ዓ.ም) ዋና ዋና አፈፃፀም እና የቀጣይ የመካከለኛ ዘመን ( 2016-2018 ዓ.ም) የልማት ዕቅዶች ላይ ያተኮረ ነው፡፡የኢኮባ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ባቀረቡት ሰነድ […]
What is Construction Industry Audit?
By Eng. Mesfin Negewo( ECA G/Director) A construction industry audit is a comprehensive examination and evaluation of the financial, operational, and regulatory aspects of a construction company or project. It is conducted to assess the effectiveness and efficiency of the company’s internal controls, risk management practices, financial management, and compliance with relevant laws and regulations. […]
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን( ኢኮባ) አመራሮችና ሰራተኞች የዛፍ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
(ኢኮባ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ኣ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን( ኢኮባ) አመራሮችና ሰራተኞች ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም የዛፍ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡በየካ ክ/ከተማ ሚሊኒየም ፓርክ ላይ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች 1500( አንድ ሺህ አምስት መቶ የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል፡፡የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ባስተላላፉት መልዕክት የዕለቱ ክንውን በሀገር አቀፍ ደረጃ “ነገን ዛሬ እንትከል”በሚል […]
በ2016 በጀት አመት የተቋም ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ የሱፐርቪዥን ስራ ተካሄደ
ኢኮባ( ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን አመራሮች የተቋሙን የ2016 በጀት አመት ዕቅድ፣ የቁጥጥር ስራ ማንዋሎች ዝግጅት፣ የቁጥጥር ስራ የሚከናወንባቸው የፕሮጀክቶች ልየታ እንዲሁም የተቋሙ የውስጥ አሰራር ዝግጅት ሂደት ላይ የሱፐርቪዝን ስራ አካሂደዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሱፐርቪዥን ስራ ላይ የዕቅድ ዘመኑ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የዕቅድና የቁጥጥር ስራ ማኑዋሎች እንዲሁም ቁጥጥር የሚካሄድባቸው […]
የኢኮባ አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡
(ኢኮባ፣ ነሐሴ 05 ቀን 2015 ዓ.ም)፡- የኢኮባ አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድን ውጤታማ ለማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ሰሞኑን አዳማ ከተማ ላይ በተካሄደው የአመራሮችና ሰራተኞች አጠቃላይ ስብሰባ ላይ የተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ግቦች እና ግቦችን ለማሳካት የተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ የተቋሙ ዕቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ለገሰ አቅርበዋል፡፡ ዕቅዱ ቀደም ሲል ከስራ […]
ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት የተሾሙት ም/ዋና ዳይሬክተሮች ከተቋሙ አመራሮች ጋር ትውውቅ አካሄዱ::
(ኢኮባ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ኣ.ም)፡- ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በመንግስት የተሾሙት ም/ዋና ዳይሬክተሮች ከተቋሙ አመራሮች ጋር ትውውቅ አካሄዱ:: ኢ/ር ደረጀ አረጋኸኝ የግንባታዎች ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር፤ ዶ/ር ሙአዝ በድሩ የምዝገባና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመንግስት በቅርቡ ተሾመዋል፡፡ አመራሮቹ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከተቋሙ አመራሮች ጋር የትውውቅ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡ የባለስልጣን ተቋሙ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማዎች […]